የ50 ቀበሌ አብሮ አደጎች እና ወዳጆች የበጎ አድራጎት ማህበር በቀድሞ ከፍተኛ 4 ቀበሌ 50 የተወለዱ ያደጉ እየኖሩ ያሉ እና በአጎራባች ቀበሌዎች ያሉ ወይም የማህበሩን ሰናይ ዓላማ የሚደግፉና የሚያደንቁ አብሮ አደጎችና ወዳጆች የመሰረቱት ህብረት ነው።
ማህበሩ:-በቀበሌው ተወልደው ያደጉ በስራ በቤት ቅያሪ ወይም በትምህርትና በስራ ወይም ከሀገር ቤት በመውጣት ምክንያት አካባቢውንና ቀበሌውን ለቀው የሄዱ የቀበሌው የዛን እና የዚህን ዘመን እኩያሞችን የሚያሰባስብ በተጨማሩም ማህበራዊ ግንኙነት የሚያጠናክር ህብረት ነው።
ይህ ማህበር
የ50 ቀበሌ አብሮ አደጎች እና ወዳጆች የበጎ አድራጎት ማህበር በቀድሞ ከፍተኛ 4 ቀበሌ 50 የተወለዱ ያደጉ እየኖሩ ያሉ እና በአጎራባች ቀበሌዎች ያሉ ወይም የማህበሩን ሰናይ ዓላማ የሚደግፉና የሚያደንቁ አብሮ አደጎችና ወዳጆች የመሰረቱት ህብረት ነው።
ማህበሩ:-በቀበሌው ተወልደው ያደጉ በስራ በቤት ቅያሪ ወይም በትምህርትና በስራ ወይም ከሀገር ቤት በመውጣት ምክንያት አካባቢውንና ቀበሌውን ለቀው የሄዱ የቀበሌው የዛን እና የዚህን ዘመን እኩያሞችን የሚያሰባስብ በተጨማሩም ማህበራዊ ግንኙነት የሚያጠናክር ህብረት ነው።
ይህ ማህበር:- ከሀገር ቤት እና ከውጪ ከሚገኙ የማህበሩ አባላት ፤በሚገኝ ወይም በሚሰበሰብ ወራዊ መዋጮና በልዩ ድጎማ ከሚገኝ ገቢ በቀበሌው የሚገኙ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሀረጋውያን ወላጅ እልባ ህፃናትን አቅም በፈቀደ መጠን ማገዝና መርዳት በተጨማሪም ስራ አጥ ለሆኑ የቀበሌው ነባር ነዋሪዎች (ወንድሞች እና እህቶች ) በዘላቂነት ራሳቸውን የሚችሉበት የስራ ዕድል መፍጠር ነው።
ጎበዝ ድሮ በግ አርደው ጠላ ጠምቀው ጠጅ ጥለው ጎረቤት ያበሉ የነበሩ ጎረቤቶቻችን ልጆቻቸውን ባመት ሁለት ሶስቴ ጊዜ ያለብሱ የነበረ አሁን ያ ሁሉ ቀርቶ የለት ኑሮን መግፋት አቅቷቸው ለሰው አይናገሩት ጨንቋቸው ቤታቸው ተሸሽገው ደግ ዘመን አምጣልን እያሉ በቤታቸው ፈጣሪን ለሚማጸኑት የቀበሌያችን ነዋሪዎች እንርዳ። መማር ሲችሉ እድሉ ላልተመቻቸላችው ታዳጊ ህጻናቶችም እንድረስ።
ይህንንም እርዳታ ለማስባሰብ በወር ሃያ $20 ከተቻለ የ12 ወር (2021 =$240) ወይንም የስድስት ወር $120 ደግሞ አቅም ከፈቀደም ከዛ በላይ እንድትረዱ በ
ጎበዝ ድሮ በግ አርደው ጠላ ጠምቀው ጠጅ ጥለው ጎረቤት ያበሉ የነበሩ ጎረቤቶቻችን ልጆቻቸውን ባመት ሁለት ሶስቴ ጊዜ ያለብሱ የነበረ አሁን ያ ሁሉ ቀርቶ የለት ኑሮን መግፋት አቅቷቸው ለሰው አይናገሩት ጨንቋቸው ቤታቸው ተሸሽገው ደግ ዘመን አምጣልን እያሉ በቤታቸው ፈጣሪን ለሚማጸኑት የቀበሌያችን ነዋሪዎች እንርዳ። መማር ሲችሉ እድሉ ላልተመቻቸላችው ታዳጊ ህጻናቶችም እንድረስ።
ይህንንም እርዳታ ለማስባሰብ በወር ሃያ $20 ከተቻለ የ12 ወር (2021 =$240) ወይንም የስድስት ወር $120 ደግሞ አቅም ከፈቀደም ከዛ በላይ እንድትረዱ በበጎ አድራጎታችን ማህበሩ ስም እንጠይቃለን።
“እኛ ሁኔታዎች ተመቻችተውልን ነገሮች ላልተመቻቹላቸው የሰፈር አዛውንቶችና ታዳጊ ህጻናቶች እንድረስ”
ውድ የሰፈራችን (ቀበሌ 50 /ውሃ ስንቁ) አብሮ አደግ ወንድሞች፣ እህቶች፣ ባገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለምትኖሩ።ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ተወልደን ባደግንበት አካባቢ ለሚኖሩ ደጋፊ የሌላቸው አረጋውያን በኑሯቸው እንዲታገዙ፣ ረዳት ለሌላቸው ህጻናት የትምህርት እድል እንዲኖራቸው፣የወጣንበትን ማህበረስብ ለማገዝ ባቋቋምነው ማህበር አላማውን ለምትደግፉ፣ የበጎ ፈቃድ ሃሳባችንን ለምትጋሩ ውዳጆቻችን ሁሉ የገንዘብ ድጋፋችሁን TD BANK በተከፈተው የባንክ አካዉንት በ Zelle 50kebele@gmail.com (use full name: Haimanot Mekoya) ገቢ እንድታደርጉ የሰባዊነት ጥሪያችንን እናስተላክፋለን።
አስተባባሪዎች
.
ከላይ የተጠቀሰው የብር መጠን በእለቱን የተለገሰን እርዳታ ላያጠቃልል ይችላል
ይሄ ፌስቡክ የሚሉት ዘመን ያመጣው የብዙኋን መገናኛ መቼም ጥቅሙ ብዙ ነው ባግባቡ ከተጠቀሙበት። የአንድ ወዳጄን ፌስቡክ አካውንት ሊንኩን ስከፍተው አንድ የማውቃት ምስል በሱ አካውንት ላይ ጓደኛው ሆና አየኋት።ትንሽ ደንገጥ ብዬ በመጠኑ አሰላስዬ ለምን አልደውልላትም ብየ በሜሰንጀር ደወልኩላት ። እሷም አላሳፈረችኝም የስልክ ጥሪውን ተቀብላ የባጥ የቆጡን አወራን ። ሬጅስተር ነርስ እንደሆነችና ዌብ ሳይት አንዳላት እንዳየውና ሰብስክሪብ እንዳደርጋት ነገረችኝ። እኔም የስልክ ጨዋታችንን እንደጨረስኩ ዌብሳይትዋን ከፍቼ ስለ ቫይታሚን “C “ ጥቅም ከዚህ ቀደም ከማውቃቸው ብርቱካን ፤ጎመን ፤ብሮክሊን ፤ በተጨማሪ ቃሪያ ይተሻለ ቫይታሚን ‘ C ‘ እንዳለው እንድያውም ቃሪያ 154mg ቫይታሚን ሲ ኮንቴንት አለው የሚል ትምህርት አገኘሁበት ።
ሆስፒአል ከገባ ሰንበትበት ያለ ጎረቤቴን ለመጠየቅ ለሁለተኛ ጊዜ አስቤ ስለነበረ እንዳለፈው ጊዜ ብርቱክን ተሸክሜ ከሚሄድ ከልጅቷ ዌብ ሳይት በተማርኩት ትምህርት ሁለት እረጃጅም ቀጫጭን ቃሪያዎች በዚፕ ሎክ ይዤ ሄድኩ። ሁለት ኪሎ ብርቱካን ከነልጣጩ ቢበል እንኳን የአንድ ቃሪይ ያክል ቫይታሚን አያገኝም እያልኩ ልጅቷን አመሰገንኩ። ሰውየው የሄንን ሁለት ቃሪያ በባዶ ሆዱ ቢበላ አምላካችን በሶስተኛ ቀን መቃብር ፈንቅሎ ሞትን እንዳሸነፈው።ይሄም ጎረቤቴ ቃሪያውን በልቶና ተፈውሶ ጉልኮሱን በጣጥሶ ከተኝበት ሆስፒታል ወደ ቤቱ ይዤው እንድሚሄድ እርግጠኛ ሆንኩ።
እንደደረስኩ የሰውየው ክፍል በፍራፍሬ ተሞልቷል። ሰውየው አልጋው ላይ የለም ለማለት ይቻላል ከስቶ። አልጋው ሌላ በሽተኛ ወይም ቤት ላጣ አሳይለም/ጥገኝነት ጠያቂ ማዳበል የችላል። ሆስፒታሉ በሽተኛው ከመክሳቱ የተነሳ አልጋውን ከግማሽ በታች ያልጋውን ስፋት መጠቀሙን አይቶ ዋጋ እንደሚቀንስለት ገመትኩ ። የተስካኩበት ጉልኮስና ኦክሲጀን ለአንድ መለስተኛ ዎርክሾፕ የኤሌትሪች መስመር የተዘረጋ ነው የሚመስልው። በጣም ከስቶ ጆሮው በቻ ነው ጎልቶ የሚታየው። ጆሮው ተለቆ ክንፍ አክሏል። ጆሮውን ቢያነቅንቅው እንደሚበር እርግጠኛ ነኝ።
አስታማሚዋ የባለቤቱ እናት ግን አምሮባቸዋል ለሱ የሚመጣውን አትክልትና ፍራፍሬ እየተመገቡ። እሱ ተሽሎት ቢወጣ እንኳን እሳቸው እሺ ብለው የሚወጡ አይምስሉም። በምቾት ወፍረው ሻሽ እንኳን እራሳቸው ላይ አረጋ ብሏቸዋል።
ከሱ ይልቅ እሳቸው እጅ እጄን አዩኝ። ባዶ እጄን እንደሆንኩ ሲያዩ የእግዚር ሰላምታውንም ነፈጉኝ። እሱም ቢሆን ሰውነቱ ይክሳ እንጂ እንደ ሬዲዮ ድምጹ ነው የቀረው። ምነው ጠፋህ አለኝ በጎርናና ድምጹ። ግራና ቀኝ ከፊትና ከኋል አየሁ ድምጹ ከሱ የወጣ አልመስልህ ብሎኝ።በሆዴ ዛሬ ይዤልህ የምጣሁት ነጭ የደም ሴልህን በአስር እጥፍ አባዝቶ ያለብህን ተውሳክ ነቅሎ የሚያውጣልህ ፍቱን መድሃኒት ነው ብዬ ለጠየቀኝ ጥያቄ አለሁ አልኩት የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶኝ ።ባለፈው ባለቤትህ መንገድ አግንቻት ነግሪያት ነበር ቢዚ መሆኔን። አልነገርችህም አልኩ።
እሷን ተዋት ይሄው መጥታ ካየችኝ ሶስት ቀን አልፏታል። መስሪያ ቤቴ እየተመላለሰች ብሞት ከመስሪይ ቤቴ የምታገኘውን ጡረታና ካሳ ስታጠያየቅ ነው የምትውለው አሉ። ድሮም ያሜሪካ ሚስት ። ካውሬ ጋር መኖር ነው አለኝ። በበሽተኛ አቅሙ በንዴት እየተውተርተረና እጅ እጄን እያየ።
እኔም ያመጣሁትን ሁለት ቃሪያዎች እራስጌው ጎን ያለ ኮሞዲኖ ላይ አስቀምጥኩ። ምንድነው አለኝ? ቃሪያ አልኩት ። ለምን ቃሪያ አመጣህልኝ? ዛሬ በዌብ ሳይት ላይ ፍቱን መድሃኒትነቱን እንፎርሜሽን አግኝቼ ነው። በቁጣ አንተና ባለቤቴ እኔን አቃጥላችሁ ልትደፉኝ ነው። የትም የሰማህውን ትርኪ ምርኪ እኔ ላይ ልትሞከር ነው? ለሶስት ሺ አመት ቃሪያ ሲበላ የኖረው እትዮጵያዊ ግፋ ቢል 45 ወይም 50 አመት ነው በህይወት የኖረው። እኔ ያልጋ ቁራኛው እንዴት ነው በቃሪያ የምፈወሰው? ብሎ ገደል ውስጥ የተቀበሩ በሚመስሉ አይኖቹ አፍጠጠብኝ። የሚስቱ እናትም ፍራፍሬ ተወዶበት ይሆናል ብለው አሽሟጠጡኝ። እኔም ያቺን ረጂስተር ነርስ በሆዴ እየረገምኩ ጥያቸው ወጣሁ። (ከፍቅሩ ተሾመ)
ጎበዝ ይህንን ጽሁፍ ጀባ ስንላችሁ ለተቸግሩት የቀበሌያችን ነዋሪዎች እርዳታችሁን አትዘንጉ።
=================================================================================
መቼም ከፍተኝ 4 ቀበሌ 50ን ለማያውቃት ከፍተኛ 4 ቀበሌ 50 አራት ማእዘን ቅርጽ ሲኖራት (ውሃ ስንቁ ሰፈር ሲባል ቅርጽና ይዞታዋን ለምግለጽ ይቸግረኛል)። 50 ቀበሌ በሶስት ዋና ዋና መንገዶችና በአንድ ወንዝ ትዋሰናለች ። በሰሜን 40 ቀበሌ ፣በደቡብ ከፍተኝ 22 ቀበሌ 02(ልደታ ቤ/ክርስቲያን)፣ በምራብ 39 እና 49 ቀበሌ(ጨፌ ሜዳ፣ናትናኤል ሆተል)፣ በምስራቅ ከፍተኝ 3 ቀበሌ 51 ( የተፈጥሮ ወንዝ፣ማሥሚዲያ) ያዋስኗታል። ሰባት የመውጫ ኬላ/በር አላት ።አራት መውጫ በሰሜን፣ሁለት በደቡብ፣ አንድ በምስራቅ የንጨት ድልድይ) ኬላ/በር አላት ።የመብራት ተደራሽነቱም እስከ 80% ይደርሳል። ግርግዳ ምሰው አንድ አምፖል ለሁለት የሚጠቀሙትን ጎረቤታሞች ሳይጨምር ነው።
በግምት 600 ሜትር ርዝመት 500 ሜትር ስፋት ሲኖራት የህዝቧም ቁጥር በግምት 2500 ይሆናል ።በውስጧ 850 የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶች ብዙ ደሳሳና በጣት የሚቆጠሩ ቪላ መሳይ ቤቶች አሉ(እኔ በነበርኩበት ጊዜ) ። አንድ የወታደር ካምፕ(መሃንዲስ መምሪያ)፣ ሁለት ሆስፒታሎች(ደ/አዝማች ባልቻና ፖሊስ ሆስፒታል)፣የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ፣አንድ የፕሮቴስታንት(መካነ እየሱስ) ቤተ ክርስቲያን፣አንድ የቀበሌ ህብረት ሱቅና ወፍጮ ቤት፣ ብስራት ሬስቶራንት፣አቶ ወርቁ ግሮሰሪ፣አሰፋ ዘይት ቤት፣ ሸምሱ ሱቅ ፣ ሁለላ ሱቅ ፣ አሊ ሱቅ፣አለሙ ሱቅ።ተካ ሱቅ፣ማዲንጎ ሱቅ፣ ሙሽሪት ሱቅ፣ፉጀጋ ሱቅ፣ አንድ በመኖርና ባለመኖር መሃል የነበረ በቅጽል ስሙ ዝንቦ ሻይ ቤት(ወደፊት የምጽፈው ገጠመኝ አለኝ)፣ ሁለት የህዝብ ውሃ መቅጃ(ቦኖ ውሃ)፣ ሶስት የህዝብ መጽዳጃ፣ አንድ እንጨት መስንጠቂያ፣ጥቂት የማይባሉ አነስተኝ ገቢ ላላቸው የለቀበሌዋ ነዋሪዎችና መጤ ጠጪዎችን የመጠጥ ጥም ለማርካት ታጥቀው የተነሱ ጠላና አረቄ ቤቶች(ሊከር ስቶር) አሏት።የልምድ ወጌሻና አዋላጆችም አሏት ።አለመታደል ሆኖ ቀበሌያቸን አንድም ጠንቋይ አልነበራትም ነበር በኔ ጊዜ።
ትምህርት ቤቶች፣ ትቸር መርሻና ፣ትቸር ፍስሃና፣ቁሪ ቄስ ት/ቤት፣ ቅ/ጊዮርጊስ ት/ቤት፣መካነ እየሱስ ት/ቤት (ኢለመንተሪ) አሏት።እሸቱ ጋራዥ፣ኮከብ ጋራዥ። ሰለሞን ጋራዥ፣ቪክቶረዮ/ጋዮ ጋራዥ አሏት።ሳንጠቀምበት ቀርተን ነው እንጂ በምስራቅ በኩል አመቱን ሙሉ የሚፈስ ወንዝ ያላት ሃብታም ቀበሌ ነበረች።የእድል ጉዳይና የበሃር በር አለመኖሯ ነው እንጂ እንደ ተቋማቷ ብዛትና አይነት እንደ ጂቡቲና ኤርትራ ሃገር መሆን ይገባት ነበር ።ቅድስቲቷ 50 ቀበሌ።
በስፖርቱም አትታማም ነበር።በውስጧ የተለያዩ ክለቦች ነበሯት። ነጻነት(ነበልባል)፣ንጋት ኮከብ፣ተርብ፣ብላክ ስታርና፣ተራማጅ ይሚባሉና ሁለት የአባቶች የጤና ክለብም ነበሩ።
ስለ አባቶች የጤና ክለብ ትንሽ ልበል።የጨዋታው ሜዳ ማርኪኒ/ ጋዮ ሜዳ ነበር የሚባለው። አሁን እርሻ ሰበል መጋዘን የሆነው።ባንድ ወቅት አባቶቻችን ይጤና ቡድን አቋቁመው ጨዋታቸውም እሁድ ማለዳ ጀምሮ ፕሮግራም አውጥተው ይጫወቱ ነበር። አብዛኞቹ የጤና ቡድን ኳስ ተጨዋቾች ኳስ ባይናቸው እንጂ በግራቸው ወይም በጃቸው ከዚህ ቀደም ነክተው አያውቁም። ማሊያቸውና ቁምጣቸው ያሁኑን ሊቨርፑልን ያስንቃሉ።የጫማቸው ነገር አይነሳ ታኬታ የሚባል ነገር የለም። የተለያየ ቆዳ ጫማ አርገው እግራቸውን ብቻ ስታየው ስራ ወይም ለቅሳ የሚሄዱ ነው የሚመስሉት።ሲጫወቱም ኳሷን የመታ ወይም የነካ እርም ይሁን ብለው የተማማሉ ነው የሚመስሉት። ብዙውን ጊዜ ኳሷን ይስቷታል።ኳሷ ለመንፈቅ ያህል አዲስ ነበር የምትመስልው። ብዙውን ጊዜ ስላልተመታች። እነሱ የሚጫወቱባት ኳስ በደብተራ(ቅስና ያፈረሰ ቄስ) የፊት ቆዳ ይተሰራች ይመሰላል። አንዳችውም በብዛት መተዋት አያውቁም። ለመምታት እግራቸውን ሲስዱና ሲስቷት የጥቂቶቹ ቁምጣ ባቱ ስር ይተረተር ነበር። በዛ ሃይል ኳሷን የመቷት ለት የተመታችውን ኳስ ወይ ልደታ ቤ/ክርስቲያን ወይ አንበሳ ጋርዥ ወይ ማስሚዲያ ወይ አቶ ዕሸቱ ወ/ማሪያም ግቢ ጀርባ በፍለጋ ነው የሚገኘው።
አንዳንዶቹ መሮጥ ከጀመሩ የሚያቆማቸው በቅርቡ ያለ አጥር ወይም ዙሪያውን የተኮለኮለው ቲፎዞ ላይ መውደቅ ነው የሚጠብቃቸው። ሲሮጡ እራሳቸውን ምቆጣጠር ስለሚቸገሩ ።ጥቂቶቹ ደግሞ እንደጆተኒ ተጫዋች እግራቸውን ገጥመው ቆመው ነበር የሚውሉት።በረኛው ሳጂን ምንም አይነቃነቁም። ከጎሉ ቋሚ አንጨት የሚለያቸው መተንፈሳቸው ብቻ ነው።በቀላሉ ወደጎል የተመታችውን ኳስ በትዝብት እያዩዋት ማዳን እየቻሉ ትገባ ነበር።ተጨዋቾቹ ምነው ሳጂን ብለው ሲቆጧቸው። አይ ተዉኝ የናንተን ቅሪላ የሚያባርር የለም ።በዚህ እድሜዬ መሬት ተንደባለል ነው የምትሉኝ ይሉ ነበር ።ሳጂን ተነስቶባቸው ኳሷ ከጠለዙ ሁለት ኳስ የጠለዙ ነው ይሚመስለው ።የጠለዙብት ጫማቸው አበሮ ወልቆ። አቶ ታዬ በጣም ጉልበት ያላቸው ተጫዋች ነበሩ።እሳቸው ወደስማይ የመቷት ኳስ ለጸሃይ ከመቅረቧ የተነሳ ቀልጣ በዛው የምትቀር ነው የምትመስለው።በስንት እግዚዮታ ኳሷ ከደቂቃዎች በኋል አልቧት ነበር ወደምድር የምትመለሰው።
የዳኛው (ባሻዬ) ነገር ነው የሚገርመው እንደ ፈጣሪ አንድም ሶስትም ናቸው(የዳኛውን፣ የሁለቱ አራጋቢዎቹን ስራ ስለሚሸፍኑ) ።ታጣፊ ወንበራቸው ላይ ቁጭ ብለው ጋቢያቸውን ለበሰው።አሜባ ሊይሳይ የሚቸል የትራኮማ መነጽራቸውን አርገው።በነገራችን ላይ መነጸራቸው በጣም አቅርቦ ከማሳየቱ የተነሳ ነገንም ያዪ ነበር፣በመነጽሩ እገዛ ትንቢት መናገር ጀምረው ነበር የወደፊቱን ስለሚያሳይ።ዳኛው ፊሽካቸውን መንፋት ነው ስራቸው ።አንዱን ፋውል የሰራውን(አቶ ተሾመን) አስጠርተው ካሁን አሁን ቀዩን ቢጫውን ካርድ አስታቀፉዋቸው ስንል። ምነው ተሾመ ዱባለ እድርተኛህ አደል እንዴ። ባለፈው አሶሳ ሄዶ ሲመለስ ወባ አሰቃይታው ሰሞኑን አሞት መነሳቱ ነው። እንዲህ በሾኬ እንደ ፊጋ በሬ የምትጥለው ነውር ነው። የሚረግፍ ጥርስ የለውም ብለህ ነው? ጥርስ ባይኖረውም የደከም አጥንቱ ቢሰበርስ፣ቢሞትብህስ ጣጣው እኮ የሁላችንም ነው ብለው ገስጠው በቃላት ማስጠንቀቂያ ይለቁታል።
እዚህ ጨዋታ ላይ ኮርና፣እጅፎሪ፣ማኖ ብሎ ነገር የለም።ያለው ህግ አስርቱን ቃላት ማክብር ብቻ ነው የሚጠበቅብህ። ጎል ከየትኛውም አቅጣጫ ማለትም ከጎሉ ፊትም ሆነ በጀርባ ከገባ በተከበሩ ዳኝ(ባሻዬ) ፊት ጎል ጎል ነው። ከተክራከርካቸው እኔ ባላይህ ፈጣሪ ያይሃል ብለው ጉዳይህን ከማትጋፋው ፈጣሪ ጋር ያያይዙብህና ተሸማቀህ ክርክርህን ታቆማለህ። ሪጎሬ(ፔናሊቲ) ባጋጣሚ ከተሰጥ መቺው አቶ ፊዳ ፎክረውና አቅራርተው ያለፉት የአያቶቻቸውን ገድል ዘርዝረው፣የበደላቸውን የቀበሌ ፍርድ ሸንጎ ረግመው ተንደርድረው የመትቷት ኳስ ነቅንቅ ሳትል እሳቸው ጎሉ ወስጥ ይገኛሉ ኳስዋን ስተዋት። አቶ ደምሴ ኳስ አንዴ ማንከባለል ከጀመሩ ቀና ብለው አያዩም።ወደ ራሳቸው ጎል ሁሉ የዘው የሄዳሉ። ቀና ብለው የራሳችውን ቡድን በረኝ ጋሽ አሰፋን ሲያዩ አይ የኔ ነገር ብልው ዩ ተርን አርገው ይመላሳሉ ።ከደከማቸው የቅረባቸው ጎል ላይ ያገቡታል፣ ጭቅጭቅ ይነሳል። ዳኛው(ባሻዬ) የትም ይግባ የት ይህ ሰው ለፍቶ ያገባው ስልሆነ ጎሉ ይጸድቃል። የሚገርመው ጋሽ ደንቁ ማሊያ ረስተው ኮትታቸውን አርገው የተጫወቱበትን ቀን አልረሳወም። የኮታቸውን ኪስ ግራና ቀኝ ይዘው ሲሮጡ ያመለጣቸውን አቶብስ ለመያዝ መንገድ ላይ የሚሮጡ እንጂ ኳስ ሜዳ ያሉ አይመስልም። አቶ ገሰሰ ኳስ የሚያቀብላቸው አጥተው ኳስ ጿሚ ሆነው ብቸኝነታቸው ያኔ አዳም ላቅመ ሄዋን ሳይደርስ ብቻውን ገነት ውስጥ ያሳለፈውን ብቸኝነት ያስታውሱኛል።አቶ እሸቱና አቶ ጌታቸው በጥሩ ሁኔታ ተቀባብለው የሳቱት ጎል የነፔሌን ጨዋት የሚያስንቅ ነበር።
በዚህ ጨዋታ ላይ የገባውን ጎል ለማውቅ ከዳኛ ይልቅ ጥሩ አካውንታንት ያስፈልግ ነበር ብዛቱ።
ይባስ ብሎ ዳኛው(ባሻዬ) ዛሬ ከበድ ያለ ጉዳይ አለብኝ ብለው ዳኝነቱን ጥለው የሄዳሉ።ከዛ በኋላ ጨዋታው በህገ አራዊት ቀኑን ሙሉ ይቀጥላል።በጨዋታው ላይ ያለው አብዋራ ፈረስ ግልቢያ ያለህ ያስመስልዋል።
ጨዋታው እንደ መደበኛው ስፖርት በ45 ደቂቃ እርፍት በ90 ደቂቃ ፍጻሜ ይሆናል ብሎ ነገር የለም። ተመልካቹ በሳቅ ፈንድቶና ሰልችቶት ጥሎ የሚሄድበት ቀን ብዙ ነው። ጨዋታው የሚቆመው አንድ ሁለት ተጫዋቾች ክፉኛ ከተጎዱና ወይ አንድ መልክተኝ ከመንደር መጥቶ ወይዘሮ እከሌ በጠና ታመው ደክመዋል ካልተባለ ንቅንቅ የሚል የለም ነበር።
በዚህ ቡድን ውስጥ የተሳተፍ አባቶቻችን በአብዛኛው በህይወት የሉም አምላክ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን።በዚህ ቡድን ላይ ተሳትፈው ስማቸውን ያላስገባሁት ሳይሳተፉም የገቡ ብዙዎች ይኖራሉ።ጽሁፉ ላይ የተጋነኑ ነገሮች አሉ፣ ለፈን ስልሆነ ከይቅርታ ጋ ዘና እንድትሉበት ነው።
ቅዲስቲቷ ቀበሌ 50 (ወሃስንቁ ሰፈር) በከተማችን ወስጥ ለልማት ተብለው ካልፈረሱት ሰፈሮች አንዷ ስትሆን ነባር ነዋአሪዎቿ በአብዛኛው ባንድ ላይ አብረው ያሉ ናቸው። በአገር ውስጥና በውጭ የምንገኝ የስፈሩ ተውላጆች ማህበር አቋቁመን የተቸገሩን/ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን በመርዳት ላይ ነን። ስለዚህ አንዳንድ ጽሁፎችን ለማዝናናትና ግንዛቤ ለመስጠት በማዘጋጀትና ለንባብ በማቅረብ ግንኙነታችንን እናጠናከር።ለወገኖቻችን የምንችለውን እንርዳ ።
እኛ ሁኔታዎች ተመቻችተውልን ነገሮች ላልተመቻቹላቸው የሰፈር አዛውንቶች፣ ወጣቶችና ታዳጊዎች እንድረስ።(ፍቅሩ ተሾመ ነኝ በሰፊው እንገናኝለን)
==================================================================================